ከፖለቲካ ገለልተኛ ባለመሆንና ከዓላማ ውጭ መንቀሳቀስ በሚል ታግደው የነበሩ ድርጅቶች ዕገዳ ተነሳ
በያሬድ ንጉሤ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከፖለቲካ ገለልተኛ አለመሆንና ከዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ዕገዳ ጥሎባቸው የነበሩ ሦስት በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ዕገዳ ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ የተጣለባቸው ዕገዳ የተነሳላቸው የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD)፣...