
በሕዳሴ ግድብ ግንባታ "15 ሺህ ሰዎች ሞተዋል" ስለመባሉ የግድቡ የሠራተኞች ደኅንነት ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በተካሄደባቸው 14 ዓመታት ውስጥ "እስከ 15 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ሞተዋል" በሚል የተጠቀሰውን ቁጥር ለረጅም ዓመታት በሂደቱ የተሳተፉ ሁለት የግድቡ የደኅንነት ባለሙያዎች ውድቅ አደረጉ። ይህንን ቁጥር አረጋግጠዋል የተባሉት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው "ጥያቄው በተሳሳተ መልኩ ተተርጉሟል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Read the full story