
አቶ ጌታቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ማህተም ከነጠቀ አካል" ጋር እንዳይደራደሩ ጠየቁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ "ለራሱ የግል እና የቡድን ጥቅም ሲባል የሕዝብን ሠላም፣ የፕሪቶሪያን ስምምነት፣ የአገሪቱን መረጋጋት እንደ መያዣ ከተጠቀመ አካል" ጋር እንዳይደራደሩ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ጠየቁ።ክፍፍል ውስጥ በገቡት የህወሓት ክንፎች ምክንያት ቀውስ ውስጥ የገባውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሚመሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን ያሉት ሐሙስ መጋቢት 4፤ 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
Read the full story