
"ወርቅ አጣሁ ብዬ ማሰብ አልፈልግም" - አትሌት ትዕግሥት አሠፋ
በጃፓን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ወርቅ አጣሁ ብዬ ማሰብ አልፈልግም አለች። በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግሥት አሰፋ 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ተከትሎ ነው ይህንን የተናገረችው። አትሌት ትዕግስት ከኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጂፕችርችር ጋር ብርቱ ፉክክር አድርጋ ነው የብር ሜዳሊያ ለአገሯ ያስገኘችው።
Read the full story