
ዩክሬን አሉኝ የምትላቸው ማዕድናት የትኞቹ ናቸው? ትራምፕስ ለምን ዓይናቸውን ጣሉባቸው?
ከዓለማችን "ወሳኝ ጥሬ ማዕድናት" ውስጥ 5 በመቶ ያህሉ በዩክሬን ይገኛሉ። ይህ 19 ሚሊዮን ቶን የተረጋገጠ የግራፋይት ክምችትን ያጠቃልላል።በተጨማሪም ዩክሬን ለባትሪዎች ቁልፍ ግብዓት የሆነው ሊቲየም፣ ከጠቅላላው የአውሮፓ ክምችት መካከል አንድ ሦስተኛው ይገኝባታል። አሜሪካ እነዚህን ለታዳሽ ኃይል፣ ለወታደራዊ መሳሪያዎች እና ለኢንዱስትሪ መሠረተ ልማት ቁልፍ የሆኑ ብርቅዬ ማዕድናት በጽኑ ማግኘት ትፈልጋለች። ለዚህ ደግሞ ከፊት የተገኘችው ዩክሬን ናት።
Read the full story