
'በመጦሪያ ዘመኔ ባዶዬን ቀረሁ'፡ ለመልሶ ልማት ያለ ምትክ ቦታ እና ካሳ ቤታቸው የፈረሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አቤቱታ
ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባ ለተለያዩ የልማት ሥራዎች በሚል መኖሪያ ቤቶች እና ተቋማት በጅምላ እየፈረሱ ነው። በተለይም ለጫካ ፕሮጀክት፣ ለኮሪደር ልማት እና ለመልሶ ማልማት ለተሰኙ ወቅታዊ የመንግሥት ትኩረቶች በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰዋል፤ ነባር የመኖሪያ አካባቢዎች ፈርሰው በሌሎች ግንባታዎች ተተክተዋል ወይም በሂደት ላይ ናቸው። በዚህ መካከል ቤታቸው ለፈረሰባቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች ካሳ እና ምትክ ቦታ የተሰጣቸው እንዳሉ ሁሉ፤ ያለምትክ ሜዳ ላይ ስለመውደቃቸው የሚናገሩትም በርካታ ናቸው።
Read the full story