
መከላከያ ሠራዊት ጄነራል ምግበይ ኃይለ ላይ ያቀረበውን ክስ የትግራይ የሰላምና የጸጥታ ቢሮ "ኃላፊነት የጎደለው ነው" አለ
የትግራይ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ብርጋዲየር ጄነራል ምግበይ ሃይለን "ለፋኖ ድጋፍ ይሰጣሉ" የሚለውን ጨምሮ ሌሎችም ያቀረባቸውን ክሶች ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲል ወቀሰ።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በፌስቡክ ገጹ፤ የትግራይ ኃይሎች አመራር የሆኑትን ብርጋዲየር ጄነራል ምግብ ሃይለን "ግብረ አበሮቹ አደራጅነትና አይዞህ ባይነት ዘመቻ አንድነት በሚል ስያሜ ፋኖ በተለያዩ ክልል የዞን ወረዳዎች ትንኮሳ ለመፈጸም ሞክሯል" በሚል መግለጫ አውጥቷል።ብርጋዲየር ጄነራል ምግበይ ሃይለ ከፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
Read the full story