
ፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስ፡ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ-ጥበብ ጥናት አድባር
የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር መርከብ ቢሆን ካፒቴኗ ፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ወልደ ጊዮርጊስ ይሆናሉ። ፕ/ር ኤልሳቤጥ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ስነ ጥበብ እና ኪነ ጥበብ ሂስ አንቱታን አትርፈዋል። ወዳጆቻቸው እና ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ብዙዎች ፕ/ር ኤልሳቤጥን 'አንቺ' ስለሚሏቸው እኛም በዛው እንቀጥል። "ወንዳዊ፣ ሰሜናዊ እና ተዋረዳዊ የኃይል ግንኙነት (hierarchical power relation) ላይ የተመሰረተ" የምትለውን እና ብዙዎች ያለ ጥያቄ እና ፍተሻ የሚቀበሉትን ዘልማዳዊ የኢትዮጵያ የታሪክ አጻጻፍ ስነ-ዘዴ ሞግታች።
Read the full story