ምሥራቅ አፍሪካ የአኅጉሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመራ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አስታወቀ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዘጋጅቶ በዚህ ሳምንት ይፋ ያደረገው እ.ኤ.አ. የ2025 የአፍሪካ ኢኮኖሚ ሪፖርት፣ ምሥራቅ አፍሪካ ከየትኛውም የአኅጉሪቷ ክፍሎች የፈጠነ ዕድገት እንደሚኖረውና በተያዘው ዓመት መጨረሻም የስድስት በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ አስታወቀ። የኢኮኖሚ ሪፖርቱ በ148...