
ጠ/ሚ ዐቢይ ለሚሾሙት ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት የትግራይ ህዝብ ዕጩ እንዲጠቁማቸው ጥሪ አቀረቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሚሾሙት ጊዜያዊ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የክልሉ ህዝብ ዕጩ እንዲጠቁማቸው ረቡዕ፣ መጋቢት 17/ 2017 ዓ.ም በግላቸው የኤክስ ገጽ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለት ዓመት ቆይታው የተጠናቀቀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚቀጥል እና "በግለሰቦች ረገድ ለውጥ ሊደረግ እንደሚችል" በቅርቡ ለፓርላማው ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ነው ይህንን የዕጩ ጥቆማ ጥሪ በትግርኛ ቋንቋ ያስተላለፉት።
Read the full story