
ለትግራይ ከሌሎች ክልሎች "በተለየ ሁኔታ" ላለፉት 11 ቀናት ነዳጅ እንዳይጫን መደረጉ ተገለጸ
የትግራይ ክልል ንግድ እና ኤክስፖርት ቢሮ ላለፉት 11 ቀናት ከሌሎች ክልሎች "በተለየ ሁኔታ" ወደ ትግራይ ክልል ነዳጅ ምንም አይነት ነዳጅ አለመጫኑን ገለጸ። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለሁሉም ክልሎች የሚያጋራው የነዳጅ ስርጭት መረጃ፤ የነዳጅ አቅርቦት ሙሉ ለሙሉ የቆመው "በትግራይ ክልል ብቻ" እንደሆነ እንደሚያመለክት በቢሮው የሸማቾች ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ክንደያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Read the full story