
ግብፅ የኬንያው ፕሬዝዳንት በሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ በመገኘታቸው ቅር መሰኘቷን ገለጸች
የኬንያ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የምርቃት ስነ ሥርዓት ላይ መገኘታቸው ግብጽን ማሳዘኑን በኬንያ የግብፅ አምባሳደር ሃተም ዮስሪ ሆስኒ ገለጹ። አምባሳደሩን ተቀብለው ያነጋገሩት የኬንያ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ በበኩላቸው፤ ግብፅ ከናይል ውሃ ጋር የተያያዘ ያላትን "ማንኛውንም ስጋት" በተመለከተ "ኢትዮጵያ ላይ ብቻ" ከማተኮር ይልቅ ከሁሉንም የተፋሰሱ አገራት ጋር እንድትመካከር ጠይቀዋል።
Read the full story