ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በገጠመው የውጭ ምንዛሪ ችግር የማምረት አቅሙ ወደ 17 በመቶ መውረዱን አስታወቀ
ከአራት ዓመታት በፊት ከብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከ(ሜቴክ) ወደ ኢትዮ ኢንጂነሪነግ ግሩፕ የተቀየረውና በታኅሳስ ወር 2017 ደግሞ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥር የሆነው የማሽነሪ ማምረቻና መገጣጠሚያው የመንግሥት የልማት ድርጅት፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘቱ...