
ከቁጥር ባሻገር፡ ነዋሪውን ከባድ ዋጋ እያስከፈለ ያለው የሁለት ዓመቱ የአማራ ክልል ግጭት
ሁለት ዓመታትን ሊደፍን የተቃረበው የአማራ ክልል የትጥቅ ግጭት ባለፉት ሳምንታት ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በግጭቱ የዕለት ተዕለት እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ የተገደበ ሲሆን፤ የትምህርት እና የሕክምና አገልግሎቶች መስተጓጎልን ጨምሮ ነዋሪው ስጋት ውስጥ ይገኛል። በስድስት ወራት 148 እናቶች እንዲሁም 70 ሰዎች በወባ በሽታ መሞታቸው ተነግሯል። ከአራት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ ሆነዋል። በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የግጭቱ ዳፋ ያልገባበት ጓዳ፤ ያልነካው ሕይወት ማግኘት ከባድ እንደሆነ ነዋሪዎች ያነሳሉ።
Read the full story