
በምንጃር ሸንኮራ የቤተ ክርስቲያን ግንባታ መሸጋገሪያ ተደርምሶ ቢያንስ የ36 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ማርያም ቤተክርስትያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ ቢያንስ 36 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ። መስከረም 21 2018 ዓ.ም. ማለዳ ከጠዋቱ 1:45 ላይ አደጋው የደረሰ ሲሆን እስካሁን ድረስ 36 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ሲረጋገጥ፣ ከ200 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Read the full story