የምግብ አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት ኃላፊዎች ዲፕሎማና ከዚያ በላይ ትምህርት እንዲኖራቸው ሊደረግ ነው
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ለምግብ አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት የቴክኒክ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖራቸው የሚያስገድድ መመርያ ሊያወጣ ነው፡፡ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኘውን የምግብ ላኪ፣ አስመጪና አከፋፋይ ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 357/2013 ለማሻሻል...