አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው ታሪፍ ለአበባና መሰል ወጪ ንግዶች ፈታኝ እንደሚሆን ተገለጸ
መንግሥት ግን ታሪፉ የበለጠ ተወዳዳሪና ትልልቅ ኩባንያዎችን ለመሳብ ይጠቅማል ብሏል በሳሙኤል አባተ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው ታሪፍ በአበባ፣ በአትክልት፣ በፍራፍሬና በዕፀ ጣዕም ምርቶች ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተገለጸ፡፡ አሜሪካ ከሁለት ሳምንት በፊት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ60 አገሮች ላይ ከአሥር...