
የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዳሴ ግድብ በሱዳን 'ጎርፍ አስከትሏል' በሚል ግብፅ ያቀረበችውን ክስ ውድቅ አደረገ
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፤ ግብፅ ሕዳሴ ግድብ "በአግባቡ ባለመተዳደሩ ምክንያት የተለቀቀ ውሃ በሱዳን ጎርፍ እንዳስከተለ" በመግለጽ ያወጣቸውን መግለጫ፤ "በሐሰት የተሞላ" እና "ተንኮል አዘል" በማለት ውድቅ አደረገ። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባይኖር ኖሮ ባለፉት ወራት በኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች የታየው "ከፍተኛ ዝናብ"፤ "ሱዳን እና ግብፅ ውስጥ በሰው ሕይወት እና በመሠረተ ልማት ላይ ታሪካዊ ውድመት ሊያመጣ ይችል" እንደነበረም ገልጿል።
Read the full story