አጎዋ በመታገዱ ከኢትዮጵያ ምርት መቀበል ያቆሙ ኩባንያዎች ለመመለስ እየጠየቁ መሆናቸው ተነገረ
ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አሜሪካ በጣለች ቀረጥ ላይ ጥናት እያደረግኩ ነው ብሏል በሳሙኤል አባተ በአሜሪካ ከኮታና ታክስ ነፃ ዕድል (አጎዋ) ዕገዳ ምክንያት ከኢትዮጵያ ምርት መቀበል ያቆሙ ኩባንያዎች እንደገና ለመመለስ እየጠየቁ መሆናቸው ተገለጸ። እ.ኤ.አ. በ2021 በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት...