
ግብፅ እና ጂቡቲ የቀይ ባሕር አስተዳደር የተጎራባች ሀገራት "ብቸኛ ኃላፊነት" እንደሆነ መስማማታቸው ተገለጸ
ግብፅ እና ጂቡቲ፤የቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ "የአስተዳደር እና የፀጥታ" ጉዳይ የውሃ አካላቱን የሚጎራበቱ ሀገራት "ብቸኛ ኃላፊነት" እንደሆነ መስማማታቸውን የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ ተናገሩ። ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም. ለይፋዊ የአንድ ቀን ጉብኝት ወደ ጂቡቲ ተጉዘው የነበሩት የግብፅ ፕሬዝዳንት አልሲሲ፤ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡማር ጊሌ ጋር ተገናኝተው ንግግር አድርገዋል።
Read the full story