በጀት የተመደበላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ አለመፈጸማቸው በፓርላማ አባላት ጥያቄ አስነሳ
በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ቃል ተገብቶላቸው፣ ታቅደው፣ በጀት ተመድቦላቸው፣ ዲዛይን ወጥቶላቸውና ተጀምረው በተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃዎች የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች አለመከናወንና አለመጠናቀቅ ለምን? በሚል በርካታ የፓርላማ አባላት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጥያቄ የተነሳው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማና መሠረተ ልማት...