የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት አምራችና አቅራቢዎች ለሥራቸው አዳጋች የሆነባቸውን ችግሮች አቀረቡ
በአገር ውስጥ የሚገኙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት አምራቾችና አቅራቢዎች፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና የጉምሩክ አሠራር ሥራቸውን አዳጋች እንዳደረገባቸው ቅሬታ አቀረቡ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአገር በቀል የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግብዓት አቅራቢዎች በተለይም ኬብል፣ ትራንስፎርመር፣ ኮንዳክተርና ሌሎች አምራቾች ጋር...