
ግብፅ የውሃ ደኅንነቷን ለማስጠበቅ አስፈላጊ እርምጃዎችን ትወስዳለች - ፕሬዚዳንት አል ሲሲ
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ገንብታ ካስመረቀችው የሕዳሴ ግድብ አንጻር ግብፅ ብሔራዊ ጥቅሟን አና የውሃ ደኅንነቷን ለማስጠበቅ አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉንም እርምጃዎችን እንደምትወስድ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ተናገሩ።ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በማስተዳደር ላይ እየተከተለችው ባለው "ኃላፊነት የጎደለው" አካሄድ ላይ አገራቸው "እጇን አጣጥፋ አትመለከትም" ብለዋል።
Read the full story