
በኦሮሚያ ምሥራቅ ቦረና ውስጥ 18 ሰዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን ባለሥልጣን ተናገሩ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ቦረና ዞን፣ ጉሚ ኤልደሎ ወረዳ 13 የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ 18 ሰዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የወረዳው ባለሥልጣን ተናገሩ። የጉሚ ኤልዳሎ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ዶዮ ዲባ፣ ታጣቂዎቹ ትናንት ሐሙስ 30/2017 ዓ.ም. ረፋድ ሦስት ሰዓት አካባቢ ከነገሌ ቦረና ወደ ጉሚ ኤልዳሎ በመኪና ሲጓዙ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎችን በማስወረድ እንዳገቷቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል።
Read the full story