
"ውጊያው ከተነሳ ውጤቱ ግልጽ ነው...ማንም አያስቆመንም"- ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
"ከማንም ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ውጊያው ከተነሳ ውጤቱ ግልጽ ነው።... ከዚያ በኋላ እዬዬ አይሠራም። አሁኑኑ አለመጀመር ማለት ነው" በማለት አስጠንቅቀዋል። "ማንም አይሞትልህም። ሞራል ይሰጥሃል እንጂ አይሞትልህም። መጨረሻ የምትሞተው አንተ ነህ፤ አያዋጣም" ብለዋል። "ከማንም ጋር ግጭት ለማድረግ ፍላጎት የለንም። ከገባን ግን ግልጽ ነው ውጤቱ። አስተማማኝ አቅም ነው ያለን ማንም አያስቆመንም። ይሄ ግልጽ መሆን አለበት። ግልጽ ነው ውጤቱ። ወደዚያ እንዳንሄድ በኃላፊነት መሥራት አስፈላጊ ይመስለኛል" በማለት ተናግረዋል።
Read the full story