የውጭ ዜጎች የመሬትና የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ
ረቂቅ አዋጁ ወቅቱን ያልጠበቀና ከሕገ መንግሥቱ የሚጣረስ ነው የሚል ተቃውሞ ቀርቦበታል የተወሰኑ አገሮች ዜጎችና ዜግነት የሌላቸው ሰዎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ይደረጋል የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመሬትና የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የመጀመሪያ ውይይት ተካሄደበት። ረቂቅ አዋጁን ለምክር ቤቱ ያስተዋወቁት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ ረቂቅ አዋጁ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት ወይም ለመኖሪያ...