
ግብፅ የኤርትራን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት በፅኑ ትደግፋለች - አል ሲሲ
ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በካይሮ ባደረጉት ውይይት ግብፅ የኤርትራን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በፅኑ እንደምትደግፍ ተናገሩ። ለአምስት ቀን የሥራ ጉብኝት ሐሙስ ጥቅምት 20 2018 ዓ.ም. ካይሮ የደረሱት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከግብጹ አቻቸው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች መወያየታቸው ተገልጿል። የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጉዞ የመጣው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ "ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ነው" በማለት ከተናገሩ በኋላ ነው።
Read the full story