
መንግሥት "በውጭ ምንዛሪ አሻጥር" የጠረጠራቸውን 112 ሰዎችን ሲይዝ ከ500 በላይ አካውንቶችን አገደ
በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የባንክ አካውንቶች መታገዳቸውን የመንግሥት የፀጥታ እና ደኅንነት አካላት አስታወቁ። የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት፣ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የክልል የፀጥታ ተቋማት በወሰዱት እርምጃ በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች እና አካወንቶች ናቸው ለእስር እና ለዕግድ የበቁት።
Read the full story