
የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር እና የዜና ሥራ አስፈፃሚ በትራምፕ ዙሪያ በተሰራ ዘጋቢ ፊልም ምክንያት ሥራቸውን ለቀቁ
የቢቢሲ ዋና ዳይሬክተር ቲም ዴቪ እና የዜና ዋና ኃላፊዋ ዴብራ ተርነስ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዙሪያ ከተሰራ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ። ሁለቱ ኃላፊዎች የፕሬዚዳንቱን ንግግር በመቆራረጥ ተመልካቾችን አሳስተዋል የሚል ትችት ከቀረበባቸው በኋላ ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ገልፀዋል። ሾልኮ የወጣ ነው የተባለው እና ቴሌግራፍ ያወጣው ጽሑፍ የፕሬዚዳንት ትራምፕ ሁለት ንግግሮች ተቆርጠው የተቀጠሉ ሲሆን፣ በዚህ ንግግርም ትራምፕ የካፒቶል ሂልን አመፅ እንደደገፉ አድርጎ ማሳየቱን ጠቁሟል።
Read the full story