
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ግብፅ ውይይትን ገሸሽ አድርጋለች፤ ከቅኝ ግዛት ዕሳቤም አልወጣችም" ሲል ከሰሰ
ታላቁ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የግብፅ ባለሥልጣኖች በተደጋጋሚ ለውይይት የቀረበ ጥሪን "ውድቅ አድርገዋል" እንዲሁም "ቀጥተኛ በሆነም ባልሆነም መንገድ ዛቻ ማድረስ ቀጥለዋል" ስትል ኢትዮጵያ ከሰሰች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ኅዳር 24/2018 ዓ. ም. ከሰዓት ባወጣው መግለጫ፤ "የግብፅ መንግሥት ወደ 21ኛው ክፍለ ዘመን መሻገር አልቻለም" ሲል ወንጅሏል። ይህ መግለጫ የወጣው የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዲላቲ፤ ግድቡን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር "ተጨማሪ ውይይት" እንደማይደረግ ለቢቢሲ መናገራቸውን ተከትሎ ነው።
Read the full story