
በቤኒን የተሞከረው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መክሸፉ ተገለጸ
እሁድ ማለዳ የምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ቤኒን ጦር ሠራዊት አባላት ሥልጣን መያዛቸውን ያስታወቁበት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መክሸፉን እና ፕሬዝዳንቱ በደኅና ሁኔታ በፈረንሳይ ኤምባሲ ውስጥ አንደሚገኙ የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። ቀደም ሲል በሌ/ኮሎኔል ፓስካል ቲግሪ የሚመራ የወታደሮች ቡድን በአገሪቱ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ባስተላለፈው መልዕክት ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን ከሥልጣን አስወግዶ የአገሪቱን ሕገመንግሥት ማገዱን አስታውቆ ነበር።
Read the full story