
በዓመት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያገኙ ቲክቶከር እና ዩቲዩበሮች "የንግድ ሥራ ገቢ ግብር" ሊከፍሉ ነው
እንደ ቲክቶክ እና ዩቲዩብ ካሉ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በዓመት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያገኙ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች፤ እንቅስቃሴያቸው "በንግድ ሥራነት" ተቆጥሮ ግብር እንዲከፍሉ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ። የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ረቂቅ ደንብ፤ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች "ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖችን" ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ያገኙትን "ሁሉንም የገቢ መጠን" የሚያሳይ "የሂሳብ መዝገብ" እንዲይዙ ያስገድዳል።
Read the full story