
የፋኖ ኃይሎች "ሰላይ ናቸው" ያሏቸውን ሦስት ሴቶች መግደላቸውን የታጣቂዎቹ አመራር አረጋገጡ
በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ኤልያስ ወረዳ ሦስት ወጣት ሴቶች በፋኖ ታጣቂዎች ተገድለው የተገኙ ሲሆን፣ አንድ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አመራር ሴቶቹ ሲሰልሉ በመገኘታቸው እርምጃው እንደተወሰደባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የደብረ ኤልያስ ወረዳ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ግድያው የተፈጸመው በቀን ሥራ ይተዳደሩ በነበሩ ሴቶች ላይ እንደሆነ እና አንዷ የመስማት ችግር ያለባት መሆኗን በመጥቀስ ፆታዊ ጥቃትም በታጣቂዎቹ ተፈጽሞባቸዋል በማለት ከስሰዋል።
Read the full story