
የአፍሪካ በሽታ መከላከል ኢቦላ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአስር የአፍሪካ አገራት ይዛመታል የሚል ስጋት መኖሩን አስጠነቀቀ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው ኢቦላ ኢትዮጵያን ጨምሮ ወደ አስር የአፍሪካ አገራት ሊስፋፋ ይችላል የሚል "ስጋት" መኖሩን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) አስጠነቀቀ። የአፍሪካ ሲዲሲ ኃላፊ ዣን ካሴያ ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ ቫይረሱ ሊሰራጭባቸው ይችላል ብለው ከዘረዘሯቸው አገራት መካከል ከኢትዮጵያ ውጭ ሁሉም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኘባቸው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወይንም ኡጋንዳ ጎረቤቶች ናቸው።
Read the full story