
"በአርሲ የሚስተዋለው በደልና ግፍ 'እስከ መቼ?' የሚል...ጥያቄን ፈጥሯል" - አቡነ ማትያስ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በምእመናን እና በአብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚፈጸመው ጥቃት መቀጠሉ "እስከ መቼ" የሚል ሐዘን እንደፈጠረ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት አስታወቁ። ባለፈው እሁድ እና ሰኞ በምሥራቅ አርሲ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች 13 የሚሆኑ ሰዎች ሲገደሉ፣ አንድ ቤተክርስቲያን በእሳት የወደመ መሆኑን እና ሌላ ቤተክርስቲያን ላይ ዘረፋ እና ጉዳት መድረሱን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና ነዋሪዎች ገልጸዋል።
Read the full story