
በትግራይ ከሥራ ቦታ፣ ከመንገድ እና ከመኖሪያ ቤት እየተካሄደው ያለው አፈሳ የፈጠረው ስጋት
በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ከሥራ ቦታቸው፣ ከመዝናኛ ስፍራ እንዲሁም ከሕዝብ ትራንስፖርት ላይ በግዳጅ ተወስደው ወደ ተለያዩ ካምፖች መላካቸውን ለቢቢሲ ትግርኛ ተናገሩ። የትግራይ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በትግራይ "የተመለመሉ" ወጣቶችን ለሠራዊት እያሰለጠነ መሆኑን ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጾ የምልመላው ሂደት ግን "በክልሉ መንግሥት እንደሚፈፀም" ተናግሯል። ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ በበኩሉ የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች በክልሉ መጠነ ሠፊ አፈሳ እና የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እያካሄደ መሆናቸውን በመጥቀስ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
Read the full story