
አሜሪካ በህወሓት መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ማዕቀብ ጣለች
አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ሰላም በማናጋት ውስጥ ተሳታፊ ናቸው ባለቻቸው አክራሪ የህወሓት አባላት እና የቅርብ የቤተሰብ አባሎቻቸው ላይ የቪዛ ክልከላ መጣሏን አስታወቀች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በአክራሪ ህወሓት አባላት እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት እንዲያገረሽ የሚያደርግ ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን በመግለጽ ይህም "በቀጣናው ያለውን ሰላም እና መረጋጋት የሚያናጋ ነው" ብሏል።
Read the full story