
የአማራ ክልል መንግሥት በግጭቱ ምክንያት ተፈናቀሉ ያላቸው ከሁለት ሺህ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ወሰነ
የአማራ ክልል መንግሥት መስተዳደር ምክር ቤት በክልሉ ከ2015 ዓ. ም. ጀምሮ በተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል ያላቸው 2,167 የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ወሰነ። በክልሉ ኮምኒኬሽን ቢሮ በኩል ይፋ የሆነው ይህ የምክር ቤቱ ውሳኔ በክልሉ የደረሰውን "ከፍተኛ" ጉዳት ጠቅሷል። መግለጫው ፋኖን በስም ሳይገልፅ "የጥፋት ኃይል" ብሎ የገለፀው ሲሆን፤ ቡድኑን "ተናግረው" የተቀላቀሉ ያላቸው ሰዎች ወደ ሰላም እየተመለሱ ነው ብሏል።
Read the full story