
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "ምክክሩን ለማስጀመር እክል" ገጥሞታል መባሉን አስተባበለ
ከአራት ዓመት ሂደት በኋላ ረቡዕ ዕለት የመጨረሻውን ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ያካሄደው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ ባለፉት ቀናት ውስጥ "ምክክሩን ለማስጀመር እክል" ገጥሞታል መባሉን አስተባበለ። ባለፉት ሦስት ቀናት ለአራት ሺህዎቹ የጉባኤው ተሳታፊዎች ስለ ሒደቱ ገለጻዎችን መሰጠቱን እና ከነገ ሰኞ አንስቶ "መቶ በመቶ" ወደ ሥራ እንደሚገባ ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
Read the full story