
ግብፅ እና ኤርትራ ቀይ ባሕርን "በሕገ ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚደረግ ሙከራን" አወገዙ
ግብፅ እና ኤርትራ የቀይ ባሕር "ደኅንነት እና አስተዳደር የሚመለከተው የጠረፉን አገራት ብቻ" እንደሆነ ገለጹ። የጠረፉ አካል ያልሆኑ አገራት ቀይ ባሕርን "በሕገ ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚደረጉት ሙከራ ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው" ሲሉም አቋማቸውን አንጸባርቀዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ በግብፅ ያደረጉት ጉብኝት “ፍሬያማ” እንደነበርም ተመልክቷል።
Read the full story