
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ወደ ሕዳሴ ግድብ የሚገባው ውሃ መቀነሱን በመግለጽ የግብፅን ክስ ውድቅ አደረጉ
በኤል ኒኖ ምክንያት ወደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገባው የውሃ መጠን "ከሚጠበቀው በታች" መሆኑን እና በዚሁም ምክንያት የግድቡን "ሙሉ አቅም በመጠቀም" ኃይል ለማመንጨት ተይዞ የነበረው ዕቅድ አለመሳካቱን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ተናገሩ። ሱዳን ኢትዮጵያ ላይ ክስ ያሰማችበት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የተቋረጠውም በአገሪቱ ባለው ጦርነት "መሠረተ ልማቱን ስላወደሙት" እንደሆነም ገልጸዋል።
Read the full story