
በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ ጥቃት አምስት ሰዎች ሞቱ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን የዞኑ ባለሥልጣን እና የሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። በሕዝብ ማመላለሻ ሚኒ ባስ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሌሎች አምስት መንገደኞች ከቀላል እስከ ከባድ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ አቀስታ ሆስፒታል መግባታቸውን የሕክምና ተቋሙ ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
Read the full story