
ህወሓት ለሦስት ወራት ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ የተሰጠው የስድስት ወር ጊዜ በመጠናቀቁ ለሦስት ወራት ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መታገዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጮ ቦርድ አስታወቀ። ህወሓት በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበ ጊዜ አንስቶ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ፣ መተዳደሪያ ደንቡን ማጽደቅና አመራሮችን መምረጥ ቢኖርበትም "ይህንን ባለማክበሩ" እግዱ እንደተጣለበት ቦርዱ ገልጿል።
Read the full story