
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ስምምነት ላይ ለመድረስ የመጀመሪያውን ዙር የቴክኒክ ድርድር አካሄዱ
ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር በተደረሰ የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት ውጥረት ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የመጀመሪያ ዙር የቴክኒክ ድርድር በቱርክ መዲና አንካራ አካሄዱ። ሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ልዩነታቸውን በሰላም ቋጭተው ስምምነት ላይ ለመድረስ በሚያደርጉት ጥረት አሸማጋይ የሆነችው ቱርክ፤ የቴክኒክ ድርድሩ የአንካራውን ስምምነት የተከተለ መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ አመልክታለች።
Read the full story