
በመተከል ዞን በተፈጸሙ ተከታታይ ጥቃቶች ምክንያት ከ40 በላይ ባለሀብቶች እርሻዎቻቸውን ጥለው ወጡ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን 20 ገደማ ሰዎች የተገደሉባቸው ተከታታይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ፤ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የቅባት እህሎችን የሚያመርቱ የግል ባለሀብቶች እርሻዎቻቸውን ጥለው ወጡ። የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ፤ በአካባቢው እየታየ ባለው ትጥቅ የተቀላቀለበት እንቅስቃሴ ምክንያት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ "45 አካባቢ" የግል ባለሀብቶች ጥለው መውጣታቸውን እንዳሳወቁት ገልጿል።
Read the full story