
ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጭ ዜጎችን ከአደንዛዥ ዕፅ ወንጀል ጋር በተያያዘ በሞት ቀጣች -አምነስቲ
ባለፈው ዓመት በሳዑዲ አረቢያ ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በውጪ ዜጎች ላይ የሚፈጸም የሞት ቅጣት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አምነስቲ ገለፀ። ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ዓመት 345 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን ይህም አምነስቲ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ነው ብሏል። ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 180 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ያለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ፣ ይህም ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።
Read the full story