
ትራምፕ በሕዳሴ ግድብ ላይ "ፍትሃዊ ስምምነት" እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል ሲሉ የግብፁ ፕሬዚዳንት አወደሱ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ በሰጡት አስተያየት "ፍትሃዊ ስምምነት" እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል ሲሉ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ አወደሱ። ትራምፕ ሰኞ፣ ሐምሌ 7/2017 ዓ.ም. አሜሪካ የ[ሕዳሴ] ግድብን አገራቸው "በገንዘብ ደግፋለች" እንዲሁም ግድቡ "ወደ ናይል የሚሄደውን ውሃ የሚዘጋ" ነው የሚሉ አወዛጋቢ ንግግር ዋሺንግተን ውስጥ ማድረጋቸው ይታወሳል።
Read the full story