
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባሉ ከአምስት ዓመት በፊት ተቋርጦ በነበረ ክስ ጥፋተኛ ተባሉ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸደቁ ሁለት አዋጆች ላይ የሕገ መንግሥት አቤቱታ ካቀረቡ ከቀናት በኋላ የታሰሩት የክልሉ ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ተሰማ፤ ከአምስት ዓመት ገደማ በፊት ተቋርጦ በነበረ ክስ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈባቸው። አቶ ዮሐንስ፤ በአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉበት ከከተማ ቦታ ሊዝ ጋር የተያያዘ ክስ፤ ከሰባት እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ ነው።
Read the full story