
በተለያዩ አካላት ከተወሰዱ ቀናት ያለፋቸው ሁለት ጋዜጠኞች እስካሁን ያሉበት እንደማይታወቅ ባልደረቦቻቸው ተናገሩ
ከጠፋ ሳምንት ገደማ የሆነው ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ቢታይም የት እንደታሰረ እንዳልታወቀ እንዲሁም ጠበቃም ሆነ ቤተሰቡም እንዲያገኝ እንዳልተደረገ ተገልጿል። ረዕቡ ዕለት "ጭንብል የለበሱ እና የወታደር ዩኒፎርም ያደረጉ በሚመስሉ" ሰዎች ተወስዷል የተባለው ጋዜጠኛ ዮናስ ደግሞ፤ ያለበትም ሆነ በየትኛው አካል እንደተወሰደ በትክክል አለመታወቁን የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ለቢቢሲ ተናግሯል።
Read the full story