
ሁለገቡ የጥበብ ሰው ደበበ እሸቱ በጥበብ እና በፖለቲካ አጋሮቹ ሲታወስ
ለረዥም ጊዜ በተለያዩ መድረኮች አብሮት የሠራው ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደበበን ሲያስታውሰው "የኪነጥበብ ሕይወታችን ለውጭው ዓለም ካስተዋወቁልን የጥበብ ሰዎች መካከል አንዱ" ይለዋል። በምርጫ 97 ዋነኛ የፖለቲካ ተፎካካሪ የነበረው ቅንጅት ለአንድነት ለዲሞክራሲ ፓርቲ ውስጥ አባል የነበረችው እና አብራው የተለያዩ የፖለቲካ ሥራዎችን የሠራችው ብርቱካን ሚደቅሳ ደግሞ "ፖለቲካን ከተለመደው መልኩ በተለየ መንገድ መሥራት የቻለ" ስትል ያላትን አክብሮት ትገልጻለች።
Read the full story